save money on electric bill

የኤሌክትሪክ ቢል ወጭን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብን?

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ዝቅተኛ የነበረ ቢሆንም በቅርብ ጊዜ በተደረገ የታሪፍ ጭማሪ ብዙ ሰው በወጭ እየተማረረ ነው። በራሳችን መንገድ የሚከተሉትን 10 መንገዶች በመከተል የኤሌክትሪክ ቢል ወጭን መቀነስ እንችላለን! እነዚህን መንገዶች በትክክል ከተጠቀምን በአማካኝ በአመት 12, 000 ብር የሚከፍል ሰው ወደ 8000 ብር እና ከዚያ በታች ዝቅ ማድረግ ይችላል። 1 . ኦድት ማድረግ – በእድሜ ብዛት የኤሌክትሪክ መስመሮች ወደ መሬት ወይም ወደ ሌሎች መስመሮች የኤሌክትሪክ ስርገት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህም የሃይል ብክነት ያስከትላል። የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና እቃዎችን በባለሙያዎች በተወሰኑ አመታት ውስጥ ማስፈተሽ ከፍተኛ የሃይል ብክነትን ይቆጥባል! 2 . እቃዎችን በሙሉ አቅም ማሰራት – አብዛኛዎቹ የኤሌክትሪክ እቃው በሙሉ አቅማቸው እና በከፊል ሲሰሩ ተመሳሳይ ሃይል ይጠቀማሉ፤ ለምሳሌ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ፓንት እና ካልሲ ሲቆሽሽ ማስነሳት እና ማጠብ ከፍተኛ ሃይል ማባከን ነው። ለትንሹም ለትልቁም ማሽኑን ከማስነሳት ማሽኑ ማጠብ የሚችለውን ያህል ልብስ በመጨመር ማጠብ ወጭን መቀነስ ነው። 3 . አምፖል መቀየር – አምፖል ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኤሌክትሪክ እቃወችን ስንገዛ ጥራት ያላቸው እቃዎች ቢሆኑ የሃይል ፍጆታቸው ይቀንሳል። LED አምፖሎችን መጠቀም ኢንካንደሰንት ( የድሮው አምፖል) ከመጠቀም 80% ሃይል ይቀንሳል። ስለሆነም LED አምፖል መጠቀም ወጭን መቀነስ ነው ። 4. የፍሪጅ ሙቀት ማስተካከል እና ፍሪጃጅን ሙሉ ማድረግ: ፍሪጃችን ሙሉ ሲሆን ያለውን የሙቀት መጠን ለረጅም ሰዓት ጠብቆ ይቆያል። ፍሪጁ ትንሽ ምግብ ከሚይዝ ሙሉ ቢሆን ውጤታማነቱ ከፍተኛ ነው፤ የምናስቀምጠው ባይኖር እንኳ በረዶ የሚሰራ ውሃ ማስቀመጥ ይመከራል። ፍሪጁ ሙሉ ሲሆን ኤሌክትሪክ ሃይል ይቆጥባል። 5. እቃዎችን ከማጥፋት መንቀል – ብዙ የኤሊክትሪክ እቃዎች ጠፍተው እንኳን አነስተኛ ሃይል የሚጠቀሙ አሉ። እነዚህን እቃዎች ከሶኬት መንቀል ወይም እንደ ብሬከር ያሉ የሃይል ማቋረጫዎችን መጠቀም የሃይል ብክነትን ይቀንሳል። 6 . የእቃ ማጠቢያ ማሽን ማድረቂያውን ማጥፋት – የእቃ ማጠቢያ ማሽን ማድረቂያው የሚጠቀመው ሃይል ከማጠቢያው ከ 15% በላይ ነው። ስለሆነም በተፈጥሮ አየር ማድረቅ ከፍተኛ ሃይል መቆጠብ ነው። 7. ማሞቂያ ማስተካከል- ማሞቂያዎች አውቶማቲክ እንድሰሩ እና በውጤታማ የሙቀጥ መጠን ማድረግ ሃይል ይቆጥባል። 8. መብራት ማጥፋት- ሌሊቱን ሙሉ ሲበሩ የሃይል ብክነት ስለሚያስከትሉ ማጥፋት ልምድ ማድረግ ወጭ መቀነስ ነው ። 9. የሶላር ቴክኖሎጅ መጠቀም- በፀሃይ ሃይል የሚሰራ ሶላር ፓኔል እና ተያያዥ እቃዎች መነሻ ዋጋቸው ውድ ቢሆኑም በረጅም ጊዜ በሚሰጡት አገልግሎት የኤሌክትሪክ ቢልን በከፍተኛ መጠን ስለሚቀንሱ ውጤታማ ናቸው! 10 . እንደምጣድ ያሉትን ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚዎች ማታ መጠቀም የኤሌክትሪክ ፍጆታን ይቀንሳል።

********* አመሰግናለሁ! Telegram: https://t.me/biksaleba

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *