ስልክዎ ቢሰረቅ ምን ያደርጋሉ?

አይበለው እና ስልካችን በሌቦች ቢሰረቅ ወይም ቢጠፋብን ወይም በሌላ ምክንያት ከእኛ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ በሌሎች ሰዎች እጅ ቢገባ ከስልኩ በበለጠ የሚያሳስቡን ብዙ ጉዳዮች አሉ። በዚህ በቴክኖሎጅ ዘመን የባንካ ገንዘባችን በሞባይላችን ነው፤ በሞባይላችን እጅግ ውድ የሆኑ መረጃዎች፣ ሚስጥሮች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የስልክ ማስታወሻዎች፣ … ወዘተ ይገኙ ይሆናል። ታድያ እነዚህን ሁሉ የያዘው ስልካችን ቢሰረቅ/ቢጠፋ ጉዳታችን ድርብርብ ነው።

ነገር ግን ለሁሉም መላ አለው! ስልካችን ቢሰረቅ ምንም እንኳን የተሰረቀውን የስልክ ቀፎ ማገኘት ባንችልም ሁሉንም ጠቃሚ መረጃዎች ግን በሰከንዶች ውስጥ መልሰን ማገኘት እንችላለን። ከጠፋው የስልክ ቀፎአችን ያሉትን ሁሉንም መረጃዎች ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንችላለን። የሰረቀውን ሰው ፎቶ ማንሳት እንችላለን። ሌባው ያለበትን ቦታ ማወቅ እንችላለን። ሲም ካርዳችን እንዳይሰራ ማድረግ እና መልሰን ከቴሌ ማውጣት እንችላለን። ይህን ሁሉ ለማድረግ የሚያስፈልገን የኢሜይላችን የይለፍ ቃል (password) ማስታወስ ብቻ ነው። ሌላው እዳው ገብስ ነው። ይህ እንድሆን ኢሜይላች እና ሌሎች ድህረ ገጾ ላይ የምንሰራቸው ማስተካከያዎች አሉ ። እነሱ አሁን እንጅ ስልኩ ከተሰረቀ በኋላ የሚሰሩ አይደሉም። ምን ማድረግ አለብን? ቀላል እና ከ 5 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ የሚወስድ ነው። ቀጥዩ ፅሁፍ ይህን ያሳያል።

ጠፋ/የተሰረቀ ስልክ መረጃ እንደት እንመልሳለን?

ምን ጊዜም ቢሆን መረጃዎቻችን በቅጅ/ኮፒ ሌላ ቦታ ቢቀመቱ የበለጠ አስተማማኝ እና ምቹ ይሆናሉ። የስልካችን መረጃዎች በራስሠር /automatically/ በጎግል ኮፒ እንዲቀመጡ ቢደረግ በርካታ ጥቅሞች ይኖሩታል። ራስ ሰር ማጠራቀሚያ (automatic Backup/ ብዙ ጥቅሞች አሉት ፤

ይኸውም፦

• አድስ ስልክ ብንገዛ ከአሮጌው ስልክ ወደ አድሱ ስልክ ምንም አይነት መረጃ መላክ ሳያስፈልገን ሁሉንም መረጃዎች በአድሱ ስልክ ማገኘት እንችላለን፤ • ስልካችን ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ ወይም ቢሰረቅ መረጃዎቹን በኮምፒዉተራችን ወይም በሌላ ስልክ ማገኘት እንችላለን፣

. ታማነትን ለማትረፍ ቤተሰብ ጋር ስልካችን ለማጋራት ያስችለናል … ወዘተ።

 ለመሆኑ መረጃዎቹ የትነው የሚጠራቀሙት/የሚከማቹት ብለን ከጠየቅን፤ መረጃዎቹ የተለያየ ቦታ ( Google, Ms, …etc) ይከማቻሉ፤ ጎግል ላይ ከጫናቸው በጎግል የይለፍ ቃላችን አማካኝነት ማገኘት እንችላለን፤ ለአንዳንድ መረጃዎች ፒን፣ ፓተርን እና ፓስዎርድ ሊያስፈልጉ ይችላሉ።

******-********-*******-******—****-******

ስልካችን እንደት ራስሠር መጠባበቂያ /automatic Backup/ ማዘጋጀት ይችላል?

ስልካችን ራስሠር መጠባበቂያ /automatic Backup/ እንዲያዘጋጅ የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች እንከተል፤ ( የተለያየ ስልክ ላይ የተለያየ መቼት (Setting) ሊኖር ይችላል፣ ) 

ለ Setting and apps ራስሠር መጠባበቂያ /automatic Backup/ ለማዘጋጀት

1. Setting > accounts and backup/manage backup setting/( system>backup) and tap on it. 

2. Manage accounts > select your best email > sync account3. On all these; contacts, calendar, people detail, drive, google fit data, Gmail.

 ለ Photo and video ራስሠር መጠባበቂያ /automatic Backup/ ለማዘጋጀት

1. Open the google photos app

2. In the menu, head to setting

3. Tab backup and sync.

4. Make sure the switch is turned on. At any time, you can visit this section and tab backup now to manually start a backup. Make sure your phone is connected to a strong wi fi network and plug it into a charger to speed up the process. Samsung galaxy offers its own backup and restore service through Samsung cloud, in my experience it is more reliable than other backup service.

**************************

የጠፋ ስልክ ማስጮህ፣ ሞቆለፍ እና መረጃ ማጥፋት

የጠፋብን/የተሰረቅነው ስልክ ወሳኝ የሆኑ የድርጅት ሚስጥሮችን ወይም የግል ሚስጥሮችን ወይም ሌሎች ለሌሎች ሰዎች የማይጋለጡ ሌሎች መረጃዎችን ሊይዝ ይችላል። እነዚህ መረጃዎች ሌሎች ጋ ሲደርሱ በእኛ ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ፣ መረበሽ እና መደናገጥ ሊያደርሱ ይችላሉ። ስለዚህ ይህን መደናገጥ የሚከላከል መተግበሪያ ላሳያችሁ፦ 

ይህ መተግበሪያ ፦

• የጠፋውን ስልክ እንዲናገኝ/ ስልኩ የት ቦታ እንዳለ/ ይጠቁመናል። 

• ስልኩን መቆለፍ ወይም ፓተርን እና ፒን መቀየር ያስችለናል፣

 • ስልኩን ማስጮህ ያስችለናል፤ 

• ስልኩ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች እንድናጠፋ ያግዘናል። 

ምን አልባት መረጃዎችን ከአጠፋን በኋላ ስልኩን ብናገኘው ከላይ ባየነው መሰረት ባካፕ ማድረግ እንችላለን። የሚከተሉት መተግበሪያዎች እነዚህን ተግባራት እንዲንከውን ያግዙናል።

**************-********

Google find my device

የመጀመሪያው መተግበሪያ Google find my device ይባላል። ይህ መተግበሪያ የጠፋው ስልካችን የት እንዳለ፣ ለማስጮህ ፣ በአድስ ፓተርን/ ፓስወርድ ለማሰር፣ መረጃው ለማጥፋት ያግዘናል። ይህን መተግበሪያ አውረደን መጫን እና በሚከተለው መሰረት መቼቱን ማስተካከል ይጠበቅብናል።

Setting> security and location> find my device> on ከሳምሰንግ ዉጭ ባሉስልኮ ይህ የሚሰራው ኢንተርኔት ሲበራ ነው። ነግር ግን ስልካችን የሰረቁ ሌቦች ቀድመው የሚያደርጉት ስልኩን ማጥፋት እና ሲሙን ማውጣት ስለሆነ የሚከተለው መተግበሪያ ከሳምሰንግ ውጭ ላሉ ጠቃሚ ነው።

 Spyic lost mobile tracker 

ይህንንም በተመሳሳይ መተግበሪያ አውረደን መጫን እና በሚከተለው መሰረት መቸቱን ማስተካከል ይጠበቅብናል።

1. Create a spyic account

 2. Download and install the spyic app

3. Click start and finish configuration process

4. You will now have access to your spyic dashboard at anytime by logging into your spyic account from the website. 

በዚህ መተግበሪያ 

• አሁን ላይ ስልካችን የት እንዳለ ፣ ወደት እየሄድ እንደሆነ በቀጥታ ማየት እንችላለን። ስልኩ እንኳን ቢጠፋ/ ባትሪ ቢዘጋ/ አሁን የት እንዳለ ማየት እንችላለን።• ይህ ስልክ የት እንደሄደ የት ቦታ ላይ ሰንት ሰዓተ ላይ ፣ ቦታውን ከሰአት ጋር ይነግረናል። 

• ሲሙ ሲቀየር ሲም መቀየሩን ይነግረናል 

Google photo- በስልኩ የተነሱ ፎቶዎችን ያሳየናል።የሌቦችን ፎቶ መውሰድ

Lockwatch የተባለው መተግበሪያ ደግሞ የስልካችን ፓተርን/ፓስዎርድ ለመክፈት ሲሞክሩ በሚስጢር ፎቶአቸውን/ አካባቢው ፎቶ በማንሳት ከአካባቢው መገኛ ጋር ወደ ኢሜይላችን ይልክልናል። 

ተጨማሪ የስልካችን መታወቂያ መዝግቦ መያዝ ጠቃሚ ነው። ሞባይላችን IMEI (international Mobile station equipment identifier) or MEID ( mobile equipment identifier) የተባለ ባለ15 ድጅት መለያ ያለው ሲሆን እስን ለማገኘት *#06# ብለን መደወል እንችላለን። ስልካችን ሲጠፋ ይህን ቁጥር ለፖሊስ እና ቴሌ በማስመዝገብ ሌሎች እንዳይጠቀሙበት ማድረግ ይቻላል!

>>>>>>>>>>>>>>>>>>><<<<<<<<<<<<<<<<<<<<

 ለተጠቀምኳቸው የእንግሊዝኛ ቃላት ይቅርታ እየጠየኩ ያነሳዋቸው ሃሳቦች መነሻ ሃሳብ እንደሰጡዋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ! 

መልካም ጊዜ!

1 thought on “ስልክዎ ቢሰረቅ ምን ያደርጋሉ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *