ብዙ ሰው ቴሌቪዥን ሲገዛ ኢንቹን እንጅ ሌላ አያይም፤ እሚገርመው አንዳንዱ ደግሞ የኢንች መጠን የሚለካው ከአንዱ ጠርዝ ወደሌላኛው ጠርዝ (ወርድ/ ቁመት) የሚመስለው አለ ። አንዳንዶች ደግሞ ብራንድ የሚያዩ አሉ፤ እኒህ ጎበዞች ናቸው ብለን ልናጨበጭብ ስንል ከስም ውጭ ብዙም አይደሉ፣ ትልቅ ብራንድ ያለው ነገር ግን ከዛ ያነሰ ብራንድ ያለው ቴሌቪዥን የሚሰጠው አገልግሎት እና ጥራት ያህል መስጠት የማይችል ቴሌቪዥን ይመርጣሉ። በዚች ፅሁፍ ቴሌቪዥን ስንገዛ ምን ምን ጉዳዮችን እንይ የሚል ምክር አዘል ሃሳብ ይዤአለሁ መልካም ንባብ!
ሚሊዮን ደቂቃዎችን ዓይናችን በመትከል የምናየውን ቴሌቪዥን ከመግዛታችን በፊት ትንሽ ደቂቃዎችን ወስደን ምን አይነት መምረጥ እንዳለብን ማንበብ ወይም መጠየቅ ተገቢ ነው።
ቴሌቪዥን ስንገዛ ማወቅ/ ማድረግ ያለብን ፯ ጠቃሚ ጉዳዮች የሚከተለውን ይመስላሉ፤
👉4K ወይም ultra HD – በምስል ጥራት ላይ ትልቅ እና ጠቃሚ ተፅኖ አላቸው። ይመረጣሉ!
👉ትልቅ የተሻለ ነው፤ ማንም ቢሆን ትንሽ ቲቪ ልግዛ ብሎ አይመኝም- ያቅም ጉዳይ ካልሆነ በቀር!
👉4K + ትልቅ= ምርጥ ቴሌቪዥን!
👉 እያንዳንዱ የምስል ነጥብ ( pixel) ማራኪ ምስል እንድያሳይ HDMI cable ጠቃሚ ነው!
👉 የድምፅ ጥራቱ የተሻለ- የውስጥ ማዳመጫው (speaker) ጥርት ያለ ድምፅ የሚያሰማ መሆን
👉 ታማኝ ብራንድ መምረጥ! የትኛዉ የቴሌቪዥን ብራንድ የተሻለ ነው? Sony, LG, Samsung ከምርጦች መካከል ናቸው!
👉 ከታማኝ ሻጮች/አከፋፋዮች መግዛት – ዋስትና ፣ ድጋፍ፣ የአገልግሎት መመሪያ ማገኘት መቻል
ምርጥ ቴሌቪዥን ለመግዛት ፯ ቀመሮች፦
፩. የቲቢ መጠን መወሰንትልቅ ትልቅ ነው፤ እንደቤታችን መጠን የምንገዛውን መጠን ቀድመን መወሰን በኋላ እንዳንፀፀት ይረዳናልማራኪ የቲቪ ሞደሎች ከቤታችን ስፋት ጋር አብረው የሚሄዱ ከ32″ እስከ 100″ መምረጥ ይቻላል። አንዳንድ ቴሌቪዥኞች ጠፍተው እንኳ በሰዓሊ ተስለው ግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ምርጥ ባለፍሬም ስዕል ይመስላሉ። ሲበሩ ደግሞ ግርማ መገሳቸው አስፈሪ ናቸው። አንዳንዶች ደግሞ ግድግዳ ላይ የተጣበኩ ማጣበቂያ (ስቲከር) ይመስላሉ። እነዚህ ደግሞ ግድግዳ ላይ በቀላሉ የሚጣበቁ ሲሆን ማስቀመጫ ለመግዛት ፈርኒቸር መሄድ አይጠበቅብንም።ልብ በሉ! 65″ ቴሌቪዥን ከ42″ ቴሌቪዥን ከእጥፍ በላይ የእስክሪን / ማሳያ ስፋት ይኖረዋል! ( እማይመስል ግን እውነት! ጅኦሜትሪ -ሂሳብ ነው)ሌላው ደግሞ የቴሌቪዥን ማያ/እስክሪን የሚለካው ዲያጎናል ፡ ከኮርነር ወደ ኮርነር ነው፥ ጎኑ አይደለም! ቁመት ወይም ወርድ አይደለም!ጠፍጣፋ ወይስ ኩርባ/የታጠፈ? ኩርባ/የታጠፈ ቅርፅ ያላቸው ቴሌቪዥኖች የጠፍጣፋዎችን ያህል የምስል ጥራት የላቸውም።
፪. የምንገዛበትን ዋጋ መጠነ ገደብ መወሰን፡ ብዙ ስናወጣ የተሻለ እንገዛለን፤ ብዙ አውጥተን ጥልቅ ጥቁር፣ የተሻለ contrast፣ ሰፊ፣ በደማቅ ቀለማት ያሸበረቀ መግዛት እንችላለን ።
፫. OLED ወይም LED መምረጥ: ሁለቱም ምርጥ ናቸው አንዱ ግን ይበልጥ የተሻለ ነው፤ OLED! ውድ ነው፣ የተሻለ የምስል ቴክኖሎጅ አለው። 4K LED እስከአሁን የማይተናነስ ምርጥ እይታ የሚሰጥ ነው። በዋጋ ግን ከ OLED ያነሰ ነው።የቲቪ ታሪክን ስናይ፦መጀመሪያ የመጣው ፕላዝማ- ይህ ቲቪ ከኋላ እብጥ ያለ ሲሆን – ለአበባ ማስቀመጫም ያገለግል ነበር፤ቀጥሎ የመጣው LCD ነው ፡ ጥሩ ነው ነገር ግን የተወሰኑ እጥረቶች አሉት። ቀጥሎ የመጣው LED በዚህ ጊዜ አብህዛኛዎቹ ቲቪ LED ናቸው።OLED የመጨረሻ ቴክኖሎጅ ነው፤ መጭውን ባናውቅም! በአጠቃላይ የምንገዛው ቴሌቪዥን LED ወይም OLED ቴክኖሎጅ ቢሆን ተመራጭ ነው።
፬. የቴሌቪዥን እይታ (resolution) መምረጥ4K ከHD በ6 ሚሊዮን ፒክስልስ ይበልጣል። ( ፒክስል ምን ማለት እንደሆነ ” ሞባይል ስንገዛ ምን ምን ጉዳዮችን ማየት አለብን ? ” በሚል ከአሁን በፊት ባቀረብኩት መረጃ ማየት ይቻላል)የበለጠ ፒክስል ያለው የበለጠ ጥራት እና ውብ ምስል መፍጠር ይችላል። የቴሌቪዥን እይታ ታሪክ፡የቆዩ ቲቪ 307200 ፒክስሎች ሲኖሩት ከዚያ ወደ 1ሚሊዮን ፒክስል (720P) ፣ ከዚያ ከ2 ሚሊዮን በላይ (1080P)፣ ከዚያ ከ2 ሚሊዮን ወደ ስምንት ሚሊዮን በላይ ( 4K)- ይቀጥላል አልቆመም ወደ 8K በዚህ አመት መጥቶአል። በአጠቃላይ 4K ከቀደሙት HD በአራት እጥፍ የተሻለ ነው።ልብ በሉ! HD (1080P) ቲቪ እርካሽ ሲሆኑ አሁንም ቢሆን እስከ 32″ ስፋት ላላቸው ቴሌቪዥኞች ማራኪ እና ውብ ምስሎችን ያሳያሉ።፭ . ከፍተኛ ፍጥነት እና ምርጥ ንፅፅር ምጣኔ ያለው (Refresh Rates and Contrast Ratios) ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው ምስላቸዉ የረጋ እና የተስተካከለ ይሆናል። ይህም ለስፖርት፣ ለተለያዩ ጨዋታዎች እና ፈጣን ምስሎች ተመራጭ ናቸው። ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ልኬት ባይኖርም የተለያዩ ብራንዶች የተለያየ የንፅፅር ምጣኔ ይጠቀማሉ።
፮. ዘመናዊነት እና ቄንጠኛማራኪ እና ዘመናዊ ቲቪዎች ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ለመገናኘት ሽቦ አይፈልጉም፤ ሽቦ አልባ ናቸው፣ ማንኛውንም በስልካችን እና በኮምፒውተራችን የምንሰራቸውን ስራዎች በእነዚህ ቴሌቪዥኖች መስራት እንችላለን። ከኢንተርኔት ጋር የሚገናኙ እና ፎቶዎች፣ ሙዚቃዎች፣ youtube፣ ወዘተ ማሳየት የሚችሉ ናቸው።
፯. HDMI Cable እና ሌሎች ተያያዥ port ያላቸው:ብዙ አማራጭ port ያላቸዉ ቴሌቪዥኖች ብልሽት ቢገጥማቸዉ እንኳን ለማስተካከል እና አማራጭ መንገዶችን ለመከተል ተመራጭ ናቸው።HDMI ጥራት ያለው እና ፈጣን ምስል ለማገኘት ወሳኝ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው።
እስካሁን ድረስ ምን ዓይነት ቴሌቪዥን መግዛት እንዳለባችሁ እርግጠኛ ካልሆናችሁ ወይም ጥያቄ ካላችሁ አስተያየት መስጫው ላይ ብትፅፉ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። መረጃውን ከወደዳችሁት ደግሞ ለወዳጆቻችሁ አጋሩ፤ ገፁን ተወዳጁ።
ስለአነበባችሁልኝ አመሰግናለሁ! በምርጥ ቴሌቪዥን ዘና በሉ!
1 thought on “ቴሌቪዥን ስንገዛ ምን ምን ጉዳዮችን እንይ?”