ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ (Hydroelectric power plant) እውነታዎች

የተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ የግድቡ አጠቃላይ መረጃ

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ 188 ሜትር ከፍታ፣ በ 350 ሜትር ጥልቀት ባለው የተፈጥሮ ገደል መሃል ላይ 450ሜ እርዝመት (ወደጎን ስፋት) ፣ ሁለት የወንዙ ማስተንፈሻ ዋሻዎች/ቦዮች፣ የመሬት ውስጥ የኃይል ማመንጫ፣ ውሃ መውጫ ዋሻዎች እና ከመቀሌ – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኤሌክትሪክ መረብ (Grid) ጋር ለማገናኘት 105 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ያለው ነው። የውሃ ማጠራቀሚያው ትልቁ ሰው ሰራሽ የውሃ አካል ነው። በአጠቃላይ 9,230 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የውሃ ማጠራቀሚያ አቅም ያለው ነው። ከ 30,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር በላይ የሆነ የተፋሰስ ቦታ (catchment area) አለው. የረጅም ጊዜ አማካኝ አመታዊ ፍሰት 3,750 ሚሜ3 ነው። በግንባታ ወቅት 3500 ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 750 ያህሉ ከአራት ሃገራት የመጡ የውጭ ዜጎች ናቸው።

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ  (Hydroelectric power plant) እውነታዎች

የተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ መገኛ

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ከመቀሌ በስተምእራብ 80 ኪሎ ሜትር አካባቢ 13° 21’ ሰሜን እና 38° 45’ ምስራቅ ሲገኝ ግድቡ በፕላቶዎች መካከል ባለ ጥልቅ ሸለቆ በደጋን ቅርጽ ወይም ኩርባ ቅስት የተገነባ ነው።

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ የተገነባው የአማራ እና የትግራይ ደንበሮ ሆኖ በሚያገለግለው የተከዜ ወንዝ ላይ ነው።

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ
ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ

የተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ የማመንጨት አቅም

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ እያንዳንዳቸው 75 ሜጋ ዋት ሃይል ማመንጨት የሚችሉ አራት ጀኔሬተሮች የተገጠሙለት ሲሆን ጠቅላላ የማመንጨት አቅሙ 300 ሜጋ ዋት ነው። በአመት 981 ጊጋ ዋት ሰዓት የማመንጨት ጉልበት አለው። ይህም ማለት አመቱን ሙሉ በአማካኝ በቀን ለ9 ሰአት በሙሉ አቅሙ ቢሰራ እንደማለት ነው ወይም በአመት ለ24 ሰዓት ለ 136 ቀናት በሙሉ አቅሙ መስራት ቢችል እንደ ማለት ነው።

ሃይል ቤት (powerhouse)

የሃይል ቤቱ ከግድቡ ግርጌ ( መውጫ ላይ) መሬት ውስጥ ባለ አለት ላይ በቀኝ በኩል የተገነባ ነው። ሃይል ቤት (ፓወር ሃውስ) የተገነባው ከመሬት በታች፣ በ68,000ሜ3 ዋሻ ውስጥ ነው። ዋሻው 98ሜ ርዝመት፣ 38ሜ ከፍታ እና 18 ሜትር ስፋት ኣለው ፣ ዋሻው በወንዙ በቀኝ በኩል ከሚገኝ ግዙፍ የኖራ ድንጋይ በመቆፈር እና በማፈንዳት የተሰራ ነው።
የሃይል ቤቱ ከባህር ወለል በላይ 970 ሜትር ላይ ሲገኝ ግድቡ ግን በባህር ወለል በላይ 1145 ሜትር ላይ ይገኛል፡ የሃይል ማሰራጫ ጣቢያው ደግሞ በቀኝ በኩል ባለ ኮረፍታ ከባህር ወለል በላይ 1300 ሜትር ከፍታ ይገኛል።

Tekeze Hydropower
Tekeze Hydropower Powerhouse

ተከዜ የውሃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ የፕሮጀክት መሠረተ ልማት

ከአገቤ ወደ ሰቆጣ መንገድ መገንጠያ ወደ ግድቡ ቦታ የሚወስደው 35 ኪሜ ቋሚ የመዳረሻ መንገድ በርታ በተባለ ኮንትራክተር የተሰራ ነው። የአሰራተኞች ካምፕ የተሟሉ 114 ቤቶች አሉት ቤቶቹም ለሠራተኞች እና ለእንግዶች ማረፊያ ናቸው። የቢሮ ሕንፃዎች ለቁጥጥር ሠራተኞች እና ለስብሰባ 120 ክፍሎች አላቸው። ከነዚህ በተጨማሪ የላብራቶሪ ሕንፃን፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የመዝናኛ ቦታዎች፣ መዋኛ ገንዳ፣ የእግር ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ እና ቴንስ መጫዎቻወች አሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *