ኦንላይ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች

የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአለማችን ላይ ኢንተርኔትን በመጠቀም ኦንላይን ምርትን፣ አገልግሎትን እና ድርጅትን ማስተዋወቅ እስካሁን ከተለመደው የማስታወቂያ መንገድ በእጅጉ ውጤታማ ናቸው።

ኦንላይን ማስታወቂያዎች በአካባቢ በተለመደው መንገድ ለሚነግዱ  ነጋደዎች  ወይም ኦንላይን ለሚሰሩ  በከፍተኛ መጠን የሽያጭ መጠንን ይጨምራሉ።  

በሃገራችን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ እና ብዙ ህዝባችን መረጃዎችን ከህትመት ሚዲያዎች (ከጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ …. ) እና መደበኛ የመገናኛ ብዙሃን (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣) ባልተናነሰ መልኩ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ስለሚያይ እና ስለሚሰማ፤  በተለይም ትንንሽ ቢዝነሶች ከህትመት ሚድያዎች ይልቅ ድጅታል ማርኬቲንግን ተመራጭ አድርጎ  መስራት ብልህነት ነው።

ኦንላይ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች በአለን  የቢዝነስ መጠን ከ100 ብር ጀምሮ እስከ ሚሊየኖች ማስታወቂያ መስራት እንችላለን። ኦንላይ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች ከወጭ/ዋጋ/ ፣ ለሚፈለገው ሰው ከመድረስ አንጻር፣የሽያጭ መጠንን ከመጨመር አንጻር ፣ ወዘተ እጅግ በጣም ተመራጭ የማስታወቂያ መንገዶች ናቸው።

ኦንላይ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች ከሚለቀቁባቸው ታዋቂ ድርጅቶች መካከል በሚከተሉት ድርጅቶች ሊሆኑ ይችላሉ

 1. Google
 2. Facebook
 3. Youtube
 4. Instagram
 5. Yahoo
 6. Email marketing

ወዘተ                                                                                                                                                     

ከእነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ተከታይ ያለው እና አብዛኛው ሰው በቀላሉ የሚያየው ፌስቡክ ሲሆን እሱ ላይ መስተዋወቅ የተሻለ ውጤታማ ያደርጋል። ጎግል እና ኢንስታግራምም ቢሆኑ ውጤታማ የማስታወቂያ መንገዶች ከሚባሉት ውስጥ ናቸው።       

ለምሳሌ አንድ ድርጅት ማስታወቂያውን በቴሌቪዥን ቢያሰራ አንደኛ ቴሌቪዥኑን የሚያየው ሰው ሁሉ የዚያ ማስታወቂያ ትክክለኛ ሰው አይደለም፣ ሁለተኛ የሚመለከተው ሰው እንኳን ሃሳቡን ለማብላላት ጊዜ የለውም መልሶ ወይም ባለበት አቁሞ መልክቱን መድገም አይችልም፣ ሶስተኛ የሚመለከተው ሰው ሌላ ስራ እየሰራ ሃሳቡን ትኩረት ሳይሰጠው መጨረሻ ላይ ብቻ ቁንጽል ሃሳብ ብቻ ሊወስዲ ይችላል፡ ተመልሶ የሚያይበት እድል የለውም። ስለዚህ ማስታወቂያው ለሚመለከተውም ለማይመለከተውም ሰው በማስተላለፍ ግምታዊ የሆነ ውጤት እንዲመጣ ያደርጋል። እውነት ነው የተሻለ ታማኝነት አለው።

በፌስቡክ እና በሌሎች የኢንተርኔት መገናኛዎች ግን ማስታወቂያው ለሚመለከታቸው አካላት ብቻ ማስተላለፍ እንችላለን። የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች ክፍያ ከሌሎቹ የሚለየው የምንከፍለው ገንዘብ የምናስተዋውቀው ነገር በደረሳቸው ሰዎች ልክ ብቻ ነው። የማይመለከታቸው ሰዎችም ማስታወቂያው አይደርሳቸውም። በማስታወቂያችን የምናካትታቸውን ሰዎች እንደት እንለያለን ካላችሁ በሚከተሉት የመምረጫ መንገዶች አንዱን ወይም በከፊል ወይም ሁሉንም መንገዶች በመምረጥ መልክታችን ማስተላለፍ እንችላለን።

 1. እድሜ ፡ ለምሳሌ ለወጣቶች የሚሆኑ ምርቶችን እድሜያቸው ክ50 በላይ ለሆኑ ሰዎች ብናስተላልፍ ትርጉም አልባ ነው። ነገር ግን ከ 18 እስከ 30 ብቻ ላሉት ብናደርግ እጅግ ውጤታማ እንሆናለን።  
 2. የመኖሪያ አካባቢ፡ ለምሳሌ አድስ አበባ እና ባህር ዳር ብቻ ልንል እንችላለን
 3. የስራ ሁኔታ፡ ለምሳሌ ኢንጅነሮች ብቻ እንዲያዩት ማድረግ እንችላለን
 4. የትምህርት ደረጃ፡ ለምሳሌ ድግሪ እና ከዚያ በላይ ያሉ ልንል እንችላለን
 5. ጾታ፡ ለምሳሌ የሴቶችን እቃ የሚያስተዋውቅ ነጋደ ለሴቶች ብቻ ማድረግ ይችላል
 6. ልምዶች፡ ለምሳሌ የኮስሞቲክስ እቃዎችን የሚሸጥ ሰው ኮስሞቲክስ አዘውትሮ የመጠቀም ልምድ ላለቸው ሰዎች እንዲሆን ማድረግ ይችላል
 7. የኢኮኖሚ ደረጃ፡ መኪና የሚያስተዋውቅ ነጋደ ለእለት ጉርሱ ለሚኖር ጉልበት ሰራተኛ ቢያስተዋውቅ ኪሳራ ነው። ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ባለሃብቶች ቢያስተዋውቅ ግን ትርፋማ ይሆናል።
 8. ሌሎችም የምንመርጥባቸው መንገዶች አለ

በአጠቃላይ ኢንተርኔትን በመጠቀም የማስታወቂያ መንገዶች እጅግ ውጤታ ናቸው።  ነገር ግን ራሱን የቻለ ሳይንስ በመሆኑ ውጤታማ የሚያደርጉ መንገዶችን ጠንቅቆ ማወቅ እና መተግበር ያስፈልጋል።

2 thoughts on “ኦንላይ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *